ዩኒዬኑ በውስጡ 73 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበር አባላትን ያቀፈ ሲሆን ከ33 ሺህ 500 በላይ አባላት አሉ።
ለዩኒዬኑ አሁን ያለው አጠቃላይ ካፒታል ከ60 ሚሊዮን 542 ሺህ በላይ ያለው ሲሆን የአከባቢው አርሶ አደሮች የግብርና ምርትና ምርታማነትን እንዲያሳድጉ በማድረግ እና በሚያቀርቡት ምርት ላይ እሴት በመጨመር የተሻለ ዋጋ እንዲያገኙ አቅዶ እየሰራም ይገኛል።
በጉባኤው የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወ/ማርያም፣ የዞኑ ም/አስተዳዳሪና የግብርና መምሪያ ኃላፊ ዶ/ር ዳንኤል ዳሌን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ አመራሮች፣ የዩኒዬኑ ስራ አመራር አካላትና አባላት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ናቸው።








