ዳሞት የወላይታ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን 72 ቶን የወላይታ ቡናን ለዓለም ገበያ በመላክ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

ዳሞት የወላይታ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን 72 ቶን የወላይታ ቡናን ለዓለም ገበያ በመላክ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

ዳሞት የወላይታ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን 72 ቶን የወላይታ ቡናን ለዓለም ገበያ በመላክ ላይ እንደሚገኝ ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ዳሳና ዋና አስታወቁ፡፡

ዳሞት የወላይታ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ማህበራት ዩኒየን 15ኛው ዙር መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተጠናቀቀ።

የበለፀገ አርሶአደርን ለመፍጠር ኅብረት ሥራ ማህበራት ያላቸውን ሁለንተናዊ አቅምን ማሳደግ እንደሚገባቸው የወላይታ ዞን ም/አስተዳዳሪና የዞኑ የግብርና መምሪያ ኃላፊ አቶ አድማሱ አወቀ አሳስበዋል፡፡

ዩኒየኑ ከዚህ ቀደም የነበረውን ድክመት አርሞ በአጭር ጊዜ ውስጥ የተሻለ ውጤት እንደሚያመጣ አቶ አድማሱ ጠቅሰው አሁን መንግስታችን የያዘውን ሁለንተናዊ የብልጽግና ጉዞና ትልም እንዲሳካ የዩኒየን ቦርድ አመራሮች፣ ሠራተኞችና አባላት መትጋት እንዳለባቸውም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የወላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል በንግግራቸው የግብርና ስራን ለማዘመንና የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ዩኒየኑ ርብርብ እያደረግ ይገኛል ብለዋል፡፡

ዩኒየኑ በዞን አስተዳዳርና በሶዶ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ በሶዶ ከተማ የወሰደውን መሬት ግንባታውን ጀምሮ እያፋጠነ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡

አያይዘውም ዩኒየኑ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የራሱን አስተዋፆኦ እያበረከት እንደሚገኝ ያሰረዱት ወ/ሮ ሰላማዊት ገበያን ለማረጋጋት ምርቱን በማሰባሰብ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያከፋፈለ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

የወላይታ ቡና ከዚህ በፊት “የሲዳማ C” በሚል ስም ሲላክ እንደነበረ ወ/ሮ ሰላማዊት አሁን የወላይታ ቡና በራሱ ስምና ብራንድ ለውጭ ገበያ የሚቀርብበትን ዕድልን መስፋቱንም አስታውቀዋል፡፡

ዩኒየን ከአባላት የተሰበሰበውን ጥራቱን የጠበቀ 72 ቶን የወላይታ ቡናን ለዓለም ገበያ በመላክ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ዩኒየን ስራ አስኪያጅ አቶ ዳሳና ዋና በአንድ ኪ/ግራም 330 የውጪ ዶላር ገቢ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡

ዩኒየን በስሩ 75 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራትን አቅፏል ያሉት አቶ ዳሳና ዩኒየን አሁን ከ93 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

የወላይታ ቡና ከሌሎች የውጭ ሀገራት ማለትም ከቢራዝልና ከኮሎሚቢያ ሀገራት እየተወዳደር እንደሚገኝም ያስታውቁት ስራ አስኪያጅ ሌሎች ምርቶችንና ፍራፍሬዎችንም ለውጪ ገበያ ለማቅረብ አቅደው እየሰራ ነው ብለዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *