ዳሞታ የወላይታ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ዩኒየን እርሻ ስራን ለማዘመን ሁለት ዘመናዊ የእርሻ ትራክተሮችን ገዥ ፈጽሟል።
August 29, 2022
የወላይታ ዞን ኅብረት ስራ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ሳሙኤል በንግግራቸው አርሶአደሩ በዘመናዊ አስተራረስ ዜዴ ተጠቃሚ እንዲሆን ታስቦና ታቅዶ የተገዛ መሆኑን ገልጸዋል።
የተገዙ ትራክተሮች የግብርና ስራን ለማዘመን ጉልህ ድርሻ እንዳለቸው የጠቆሙት ወ/ሮ ሰላማዊት በተለይም የበጋ መስኖ ስራ የላቀ ጠቀሜታ እንዳለውም አስረድተዋል።
አያይዘውም ዩኒየን አባላት ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም አባላት ላልሆኑም ጭምር ከመንግሥት አካላት ጋር በመነጋገር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋልም ብለዋል።
ለዩኒዬኑ ማህበር አባላትና ሌሎች በወላይታ አከባቢው ለሚገኙ አርሶአደሮች በዩኒየኑ ውል መሰረት በተመጣጣኝ ዋጋ እንደሚከራይም ተገልጿል።
ዩኒየኑ በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የራሱን አስተዋፆኦ እያበረከት እንደሚገኝ ያሰረዱት ወ/ሮ ሰላማዊት ገበያን ለማረጋጋት ምርቱን በማሰባሰብ ለማህበረሰቡ በተመጣጣኝ ዋጋ እያከፋፈለ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡
የዩኒየኑ አባላት ከዚህ በፊት በማካናይዘሽን ስራ ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የገለፁት የቴክኖሎጂ አቅርቦት ውስንነትን ለመቅረፍና የግብርና ሥራን በዘመናዊ መንገድ በመከወን ምርታማነትን ለማሳደግ ያግዛሉ ብለዋል፡፡
ስራ አጥ ወጣቶች በገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ተደራጅተው ለሚሰሩት የተገዛው የእርሻ መሣሪያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይደረጋል ብለዋል።
የዩኒየን ቦርድ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደምሴ ዳና በበኩላቸው የበለፀገ አርሶአደርን ለመፍጠር ኅብረት ሥራ ማህበራት ያላቸውን ሁለንተናዊ አቅምን በማሳደግ በቁርጠኝነት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
የግብርና ስራን ለማዘመንና የአርሶአደሩን ምርትና ምርታማነቱን ለማሳደግ ዩኒየኑ ርብርብ እያደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡
ዩኒየን በስሩ 75 መሠረታዊ ኅብረት ሥራ ማህበራትን አቅፏል ያሉት አቶ ዳሳና ዩኒየን አሁን ከ270 ሚሊዮን ብር በላይ ካፒታል ማፍራት መቻሉንም አስረድተዋል፡፡

